የኅዋ ሰሌዳችን በጥገና ላይ ስለመሆኑ - ማስታወቂያ!

Website Maintenance Notice

መስከረም ፩፡ ፪ሺ፲፱ ዓ.ም.

ልዑል እግዚአብሔር፡ ከዘመነ ማርቆስ፡ ወደዘመነ ሉቃስ አሸጋግሮ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ኢትዮጵያን፡ የ፯ሺ፭፻፲፱ (የሰባት ሽህ አምስት መቶ ዐሥራ ዘጠነ)ኛውን ዓመተ-ልደቷንና የነጻነት ህልውናችንን በዓል እንኳን በያለንበት በሰላም አደረሰን!

ለክቡራን ኪዳናውያትና ኪዳናውያን የማኅበረሰባችን አባላት በሙሉ፤

«ኢትዮጵያ የእግዚአብሔር መንግሥት መኾኗን፣ ኢትዮጵያውያትና ኢትዮጵያውያንም የቅዱሱ ኪዳን ሕዝብ መኾናቸውን ለማስረዳትና የኢትዮጵያንና የኢትዮጵያውያንን የኾነውን ኹሉ ለመጠበቅና ለማስጠበቅ» ለሚለው መለኮታዊ ዓላማ ሲያገለግል የቆየው የኅዋ ሰሌዳችን (Website)፤ በዘመናዊ መልኩ ተዋቅሮ አገልግሎቱን ይበልጥ ለማሳደግ የቴክኒክ ማሻሻያና የጥገና ሥራዎች እየተደረጉለት ይገኛል።

አዲሱ የኅዋ ሰሌዳችን እንደ ጭን መቀመሪያ (Laptop/Desktop) እና የኪስ ስልክ ባሉ መሣሪያዎች ላይ ብቅዓትና ጥራት ባለው መልኩ አገልግሎት እንዲሰጥ፣ እንዲሁም በተለያዩ የኅዋ ዐውታር መጐብኛዎች (Browsers) ላይ የኢትዮጵያኛ (ዐምሓርኛ) ሆሄያትን ያለምንም ችግር ለቅሞና አጣርቶ ማንበብ እንዲያስችል ተደርጎ እየተዘጋጀ ይገኛል። በተለይም በድምፅና በሥዕል የሚተላለፉትን መልእክቶች በቀላሉ ለመስማትና ለመመልከት የሚያስችል ይሆናል።

ይሁን እንጂ ይህ የጥገና እና የማሻሻያ ሥራ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ አገልግሎት ላይ እስከሚውል ድረስ፣ ተጠቃሚዎች የኅዋ ሰሌዳውን አስቀድሞ በነበረበት መጠንና ሙሉ ደረጃ ለመገልገል እንደማይቻል በአክብሮት እንገልጻለን።

በዚህ የጥገና ወቅት ሊፈጠር በሚችለው አለመመቸት ከልብ የመነጨ ይቅርታችንን እየጠየቅን፣ ሥራው ተጠናቆ በይፋ እስክንመለስ ድረስ በትዕግሥት እንድትጠባበቁን በአክብሮት እንጠይቃለን።

ወደፊት በመደበኛነት ከምንጠቀምባቸው ከግእዝ፣ ከኢትዮጵያኛና ከእንግሊዝኛ ቋንቋዎች ባሻገር መልእክቶቹን ወደተለያዩ አገሮች ቋንቋ ተርጉመን የምናቀርብ ሲሆን፤ በቍጥር ፪/፳፻፮ ዓ. ም. ባስተላለፍነው የነጋሪት ቃል መሠረት ከእኛ ጋር ለመሥራት የምትፈልጉ ኪዳናውያን ፍላጎታችሁን እንድታሳውቁን እንጋብዛለን።

«ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት መኾኗንና ኢትዮጵያውያትና ኢትዮጵያውያንም፡ የእግዚአብሔር ልጆች የመኾናቸውን» እውነታ፡ ለዓለሙ ለማዳረስ፡ በምናደርገው ሓዋርያዊ ገድል፡ ይህ የኅዋ ሰሌዳ፡ እናንተን ለማገልገል፡ እጅግ አመቺና ቀልጣፋ ኾኖ እንደሚገኝ እናምናለን።

11 September 2026

In the Service of Ethiopia, the Kingdom of God!

Our website, dedicated to the divine mission of "demonstrating that Ethiopia is the Kingdom of God and Ethiopians are the people of the Holy Covenant, and protecting all that belongs to Ethiopia and Ethiopians," is currently undergoing essential updates and technical maintenance to upgrade its services.

The newly restructured website is designed to be fully responsive and optimized for various devices, including laptops and smartphones. It will ensure seamless rendering of the Ethiopian (Amharic) script across different web browsers and offer an easier way to access our audio and visual messages.

Please note that Until these technical upgrades are fully completed, users will not be able to access the website at its full capacity or use it as previously structured.

We sincerely apologize for any inconvenience this temporary disruption may cause and kindly ask for your patience and understanding as we finalize this work to serve you better.

In addition to our standard languages, Ge'ez, Amharic, and English, we plan to translate our content into various global languages in the future. In accordance with the Proclamation (Negarit) No. 2/2006 E.C., we invite any covenant members who wish to collaborate with us to express their interest.

Thank you for your continued patience.

Divine Blessings.

In the Service of Ethiopia the Kingdom of God,
The Covenantal Brothers and Sisters of Nibure-Id Ermias Kebede Wolde-Yesus.

Attachments / አባሪዎች:

📄 የ፳፻፲፱ ዓ.ም ኪዳናችን ቀን መቊጠሪያ. 📄 የ፳፻፲፱ ዓመተ ምሕረት መልእክት