ቍጥር ፲፰/፳፻፱ ዓ. ም. ቃለ-ዐዋድ።
ቃለ ዐዋድ!
እምኢትዮጵያ፡ ዘመንግሥተ እግዚአብሔር።
የአዋጅ ቃል!
ከኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት።
ለዚህ፡ የዐዋጅ ቃል፡ መነሻ የኾነው ምክንያት፡ ለእውነተኞች ልጆቻችን፡ ለመናገርም፣ ለመስማትም፡ ሊያሠቅቋችሁ የሚችሉ፣ ነገር ግን፡ ሓሰት በመኾናቸው፡ በእኛዪቱ እግዚአብሔራዊት እውነት፡ አማናዊነታቸው የተነገረላቸው ኹለት ቍም-ነገሮችን ስለያዘ፡ አርእስተ-ጉዳይ ነው፤ እርሱም፦
፩ኛው፡ "ገድለ-አዳም" በሚል ርእስ፡ አብነቱ የኾነውን ግእዙን፡ ወደኢትዮጵያኛ [ዐማርኛ] የተረጐመው፡ "መምህር ተስፋ-ሚካኤል ታከለ" የተባለ ሰው ኾኖ፡ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/በሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ፣ ማኅበረ-ቅዱሳን፣ በ፳፻፰ ዓ.ም. ታትሞ በተሠራጨ መጽሓፍ ውስጥ፡ ቅዱሱን የባል እና ሚስት ሩካቤ-ሥጋን ምግባር፡ "የእኛን የእግዚአብሔርን ሕግ እንደማፍረስ የሚያስቆጥርና ራሱም፡ እንደዝሙት የሚቆጠር፡ የኃጢኣት ግብር ነው!" በሚያሰኝ አገላለጽና አቀራረብ፡ የሩካቤ-ሥጋን አደራረግና አፈጻጸም፡ ለአዳም እና ለሔዋን ያሳዩዋቸውና ያስተማሯቸው "ሰይጣናት ናቸው!" የሚለው ሓሳዊና እኩይ፡ ነገረ-ጽሕፈት ነው።
፪ኛው፡ ''በቅዳሴ ጊዜ፡ ወዲያና ወዲህ እየተመላለሱ ያወኩትን፡ ሕፃናተ- ገምኑዲን 'አጥፉ!' ብለን፡ እኛ እግዚአብሔር፡ መላእክትን እንደሰደድን፣ የቀሩት መላእክት፡ የተላኩበትን ግዳጅ ፈጽመው ሲያርጉ፡ 'ቀውስጦስ' የሚባለው አንዱ መልአክ ብቻ፡ አንዱን መልከ-መልካም ሕፃን ከነማርዳው አግኝቶ፡ 'ይህንስ፡ የፈጠረው ይግደለው!' ብሎ ሳይቀሥፈው ስለተወው፡ በዚህ የተልእኮ ጉድለቱ፡ መልአካዊው ኃይል ተነሥቶት፡ ማረግ ሳይቻለው በመቅረቱ፡ በእኔ ተማሕፅኖ፡ መለኮታዊዉን ምሕረት አግኝቶ፡ እንደገና፡ ወደሰማይ የማረግ ብቅዓቱ እንደተመለሰለት ተደርጎ፣ በቅዳሴ ማርያም፡ የአንድምታ ትርጓሜ መጽሓፍ ውስጥ የተተረከው፡ ዝክረ-ነገር ነው፤
ጥያቄዎችና፡ መልስ ኾነው የተጠቃለሉት ዓበይት ቍም-ነገሮች
፩ኛ. ከላይ ለተወሳው ኹሉ፡ የአይሁድና የግብፃውያን ጠንቀኛ ክፉ ግብር፡ ቀዳሚው ማስረጃ
፪ኛ. የኖኅ እና የካም እውነተኛ ማንነት
፫ኛ. ለ"ገድለ-አዳም" ድርሳናቸው፡ ሓሳዊ ጥቅስ፡ አጠቃላይ መልስ
፬ኛ. "ሕፃናተ-ገምኑዲን ፍጁ!" ተብለው የተላኩትን መላእክት በሚመለከት
፭ኛ. ሕፃናት፡ በእግዚአብሔር ዘንድ ያላቸው ቅርበት፣ ስለእነርሱም የተናገረላቸው ቃላት
፮ኛ. "ሕፃናተ-ገምኑዲን ፍጁ!" ተብለው ከተላኩት መላእክት፣ አንዱ የኾነው፡ የቀውስጦስ፡ እውነተኛ ዝክረ-ነገር
መልእክቱን፡ በሙሉ ለመከታተል፡ እንደሚከተለው ይቀጥሉ!...