አሥሩን ቃላት የያዘችው ጽላት፡ ገና አዳምና ሔዋን ሲፈጠሩ ስለመኖሯ ምን ማረጋገጫ አለ?
Submitted by etkog12 on Sat, 03/26/2016 - 19:50
“የመጀመሪያዋ ሰንበት”፡ ከኹለተኛዋና ከዘላለማዊቷ “ሰንበተ ክርስቲያን” በፊት፡ አስቀድማ የነበረች መኾኗን ለመግለጽ፡ “ቀዳሚት ሰንበት” ወይም “ቅዳሜ” የሚለው ስያሜ ያረጋግጣል። እንዲህ አድርጋ፡ ኹለቱን ሰንበታት፡ በየመልካቸውና በየማዕርጋቸው የምታከብረው፡ ኢትዮጵያ ብቻ በመኾኗ፡ በዓለም ላይ ካሉ ሃይማኖቶችና አብያተ ክርስቲያናት መካከል፡ እርሷ ለያዘችው ቀዳሚነት፡ አንዱ ማስረጃ፡ ይህ መኾኑን ማስተዋል ይገባል።
ኋላ፡ እግዚአብሔር፡ ታቦተ ጽዮንን፡ ከእስራኤላውያን እጅ አውጥቶ፡ በባለአደራነት፡ ለእነርሱ፡ ለኢትዮጵያውያን እንድትሰጥ ያደረገው፡ አንዱም፡ በዚሁ፡ በኪዳነ ልቦና ይፈጽሙት በነበረው፡ ንጽሕ አምልኮታቸው ምክንያት መኾኑ፡ ሊታበል ከቶ አይቻልም። ይኽም እውነታ፡ ዓለም በተቀበላቸው፡ ቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ስማቸው በተመዘገበው፡ በመልከ ጼዴቅ፥ በዮቶርና በንግሥት ሳባ ሃይማኖት፥ አምልኮና ምጋባር ተረጋግጦ ይታወቃል።
(ለተጨማሪ ማብራሪያ ኢትዮጵያ፡ የዓለሙ መፋረጃ! ከገጽ ፸፯ ጀምሮ ይመልከቱ)