የ፳፻፯ ዓ.ም. የደብረ ታቦር (ቡሔ) በዓል መልእክት።

እግዚአብሔር አብወእም፡
እንኳን፡
ልጃቸው ኢየሱስ መሢሕ፡ በግርማ መለኮቱ ተገልጾ የታየበትን፡
የደብረ ታቦርን በዓል፥
ዘንድሮም፡ በ፳፻፯ተኛው (በኹለት ሺ ሰባተኛው) ዓመተ ምሕረት፡
በያለንበት፡ በደኅና አድርሰው፡ በሰላም ለማክበር አበቁን!

+ + +

የደብረ ታቦር (ቡሔ) በዓል።

     ለእኛ፡ ለቅዱሱ ኪዳን ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፡ ከዓበይት በዓሎቻችን፡ አንዱ የኾነው፡ በዓለ ደብረ ታቦር የሚውለው፡ በነሓሴ ፲፫ ቀን በመኾኑ፡ ለጾመ ፍልሰታ ሱባዔ፡ ልዩ ምዕራፍ ኾኖ፡ በታላቅ መንፈሳዊ ተመስጦና ማኅሌት ይከበራል።
     ይህ በዓል፡ መድኅናችን ኢየሱስ መሢሕ፡ በዐጸደ ሥጋ፡ ዐብረውት ከነበሩት ደቀ መዛሙርቱ መካከል፡ ጴጥሮስንና ያዕቆብን፥ ወንድሙንም ዮሓንስን፥ በዐጸደ ነፍስ ካሉት ባለሟሎቹ ደግሞ፡ ሙሴንና ኤልያስን፡ ከኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ በሚገኘው፡ "ታቦር" በተባለው፡ የወይራ ዛፍ ተራራ ላይ አምጥቶ፡ የባሕርይ አምላክነቱን በመግለጥ፡ ታማኞች አገልጋዮቹ፡ ሊያዩ የተመኙትን፡ እንዲያዩ፥ ሊሰሙ የተመኙትንም፡ እንዲሰሙ ያደረገበት ቸርነቱና ኃይሉ የሚዘከርበት ነው።
     ይህንም፡ እርሱ፡ ለሕዝቡ፡ በምሳሌ ያስተምራቸው የነበረው፡ ነቢዩ ኢሳይያስ፡ "እስመ እንዘ ይሬእዩ፡ ኢይሬእዩ። ወእንዘ ይሰምዑ፡ ኢይሰምዑ፤ ወኢይሌብዉ።"
     ማለትም፡ "እያዩ፡ ስለማያዩ፥ እየሰሙም፡ ስለማይሰሙ፣ ስለማያስተውሉም" ወገኖች፡ የተናገረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ መኾኑን፡ መድኃኒታችን፡ ለደቀ መዛሙርቱ ጥያቄ፡ መልስ በመስጠት ያስረዳቸው ቃሉ፡ በሥርዓተ ቅዳሴ ጸሎት ላይ፡ ዘወትር ይወሳል።
     ይህም፡ "ወለክሙሰ፡ ብፁዓት አዕይንቲክሙ፡ እስመ ይሬእያ፤ ወዕዘኒክሙ፡ እስመ ይሰምዓ። አማን እብለክሙ! ከመ ብዙኃን ነቢያት ወጻድቃን፡ ፈተዉ ይርአዩ፡ ዘትሬእዩ፤ ወኢርእዩ። ወፈተዉ ይስምዑ፡ አንትሙ ዘትሰምዑ፤ ወኢሰምዑ።"
     ማለትም፡ "የእናንተ ግን፡ ዓይኖቻችሁ ስለሚያዩ፥ ጆሮዎቻችሁም ስለሚሰሙ፡ ብፁዓት ናቸው። እውነት እላችኋለሁ! ብዙዎች ነቢያትና እውነተኞች፡ እናንተ፡ ዛሬ የምታዩትን፡ ሊያዩ፡ እጅግ ፈልገው ነበር፤ ነገር ግን፡ አላዩም። እናንተ፡ ዛሬ የምትሰሙትንም፡ ሊሰሙ፡ እጅግ ፈልገው ነበር፤ ነገር ግን፡ አልሰሙም።" ሲል፡ ለደቀ መዛሙርቱ የተናገረው ነው። (ማቴ. ፲፫፥ ፲፫-፲፯።) 

ሙሉውን ንባብ ለመመልከት፡ እንደሚከተለው ይቀጥሉ!

     የቡሔ ዳቦ፡ እግዚአብሔር እም ድንግል ማርያም፡ ''ገራህተ ሙሴ'' ማለትም፡ ''የሙሴ እርሻ'' ተብላ፡ ላስገኘችው፡ ለአማናዊው የቡሔ ኅብስት፡ ኢየሱስ መሲሕ፡ ምሳሌው ነው!

ሥዕሉን ለመመልከት ፡ እንደሚከተለው ይቀጥሉ!