Messages
ይድረስ፦ በምድርና በሰማያት በመላችው፡ በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ዕቅፍ ውስጥ፡ የእግዚአብሔርና የኢትዮጵያ ልጆች፣ ነጋሢዎችና ካህናት ኾናችሁ፥ «ኢትዮጵያ» በተባላችው የዐፅመ ርስት አገራችሁ ሠፍራችሁ፥ በኪዳናዊው ኢትዮጵያዊ የጨውነት ህልውናችሁና የመብራትነት ተልእኳችሁም፡ አልጫና ጨለማ በኾነው፡ በዓለሙ ኹሉ አህጉራት፡ በመለኮታዊው ዕቅድ ተዘርታችሁና ተሠራጭታችሁ፣ ተልካችሁና ተመድባችሁ፡ በቀዳማዊቷ የትንሣኤና በዘለዓለማዊቷ የሰንበት ሕይወት ለምትኖሩ፡ የቅዱሱ ኪዳን ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ወገኖቻችን ለኾናችሁት፡ ኪዳናውያን ወንድሞችና ኪዳናውያት እኅቶች ኹሉ! በያላችሁበት! በእግዚአብሔር አብወእም ድንግል ማርያም፥ በእግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ መሲሕ እና በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ስም፡ ኢትዮጵያዊውን ሰላምታችንን፡ እናቀርብላችኋላን። |
ልዑል እግዚአብሔር፡ እንኳን፡ ለ፪ሺ፲፫ (፳፻፲፫`)ኛው ዓመተ ምሕረት፡ ጾመ ፍልሰታ ለማርያም፡ በያለንበት፡ በደኅና አድርሶ፡ የምስጋና ሱባዔያችንን፡ ለመጀመር አበቃን! እኛ፡ የዛሬዎቹ ኪዳናውያንና ኪዳናውያት የኢትዮጵያ ልጆች፡ ቸሩ ፈጣሪያችን፡ በሰማይም፥ በምድርም፡ በፍጥረተ-ዓለሙ ኹሉ ላይ በሰፈነችውና የእግዚአብሔርዋ መንግሥት በኾነችው ኢትዮጵያ አገራችን ውስጥ፥ በመላውም ዓለም ተሠራጭተን እየኖርን ባሳለፍነው የሕይወትና የጤንነት ህልውናችን፡ ዓመቱን ሙሉ አቆይቶን፡ እነሆ፡ ከዚህ የምስጋና ሱባዔያችን ለመድረስ አብቅቶናልና፡ እናመስግነው! ይህችኑ፡ የዘንድሮዋን የፍልሰታ ጾማችንን፡ እንደተለመደው፡ እያንዳንዳችን፡ እንደየዓቅማችን፡ ስለራሳችንና ስለወገናችን፥ ስለአገራችንም ብቻ ሳይኾን፡ ስለዓለሙ ኹሉ ደኅንነት ጭምር፡ በእውነተኛ ንስሓ ተመልሰንና በሱባዔ ተጠምደን፡ በምናካኺደው የምስጋና ጾም-ጸሎታችን የምንፈጽማት፡ በአዲሱ መለኮታዊ የዐዋጅ ቃል መንፈስና ዘመን ይኾናል። |
ለእኛ፡ ለቅዱሱ ኪዳን ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፡ ከዓበይት በዓሎቻችን፡ አንዱ የኾነው፡ በዓለ ደብረ-ታቦር የሚውለው፡ በነሓሴ ፲፫ ቀን በመኾኑ፡ ለጾመ ፍልሰታ ሱባዔ፡ ልዩ ምዕራፍ ኾኖ፡ በታላቅ መንፈሳዊ ተመስጦና ማኅሌት ይከበራል። ይህ በዓል፡ ከመድኃኒታችን፡ ከእግዝእትነ [እግዝእተብሔራችን] እም፡ ድንግል ማርያም፡ በሰውነት የተወለደው፡ ሰላማችን እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ መሲሕ፡ በዐጸደ ሥጋ፡ ዐብረውት ከነበሩት ደቀ መዛሙርቱ መካከል፡ ጴጥሮስንና ያዕቆብን፥ ወንድሙንም ዮሓንስን፥ በዐጸደ ነፍስ ካሉት ባለሟሎቹ ደግሞ፡ ሙሴንና ኤልያስን፡ ከኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ በሚገኘው፡ "ታቦር" በተባለው፡ የወይራ ዛፍ ተራራ ላይ አምጥቶ፡ የባሕርይ አምላክነቱን በመግለጥ፡ ታማኞች አገልጋዮቹ፡ ሊያዩ የተመኙትን፡ እንዲያዩ፥ ሊሰሙ የተመኙትንም፡ እንዲሰሙ ያደረገበት ቸርነቱና ኃይሉ የሚዘከርበት ነው። መልእክቱን በሙሉ ለመከታተል፡ እንደሚከተለው ይቀጥሉ!.. |
ፍልሰታሃ ለማርያም! ነሓሴ ፲፮ ቀን የሚከበረው፡ የቅድስት ድንግል ማርያም፡ ወደሰማይ የመፍለሷ በዓል። አግሃደት ፍልሰታሃ፡ ማርያም ድንግል! ልዑል እግዚአብሔር፡ሃይማኖታችንና አገራችን፥ እናታችንና ንግሥታችን፡መድኃኒታችን እግዚአብሔር እም፡ ቅድስት ድንግል ማርያም፡ ከምድር ወደሰማያት የተመለሰችበትን፡ የፍልሰቷን በዓል፡ ዘንድሮም፡ በ፳፻፲፫ተኛው (ኹለት ሽህ፡ ዐሥራሥስተኛው) ዓመተ-ምሕረት፡ በያለንበት፡ በደኅና አድርሶ፡ እንኳን፡ በሰላም ለማክበር አበቃን! መልእክቱን በሙሉ ለመከታተል፡- |
ልዑል እግዚአብሔር፡ ከዘመነ ማቴዎስ፡ ወደዘመነ ማርቆስ አሸጋግሮ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ኢትዮጵያን፡ መልእክቱን በሙሉ ለመመልከት፡ እንደሚከትለው ይቀጥሉ!... |
ከመስከረም ፩፡ ርእሰ-ዐውደ-ዓመት፡ እስከኅዳር ፳፩ ቀን፡ ተዝካረ-ማርያም ድረስ ስላሉ በዓላትና አጽዋማት፡ መልእክታዊ ማብራሪያ። የእግዚአብሔር እም፡ ቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ልደት። [በግእዙ፡ "እግዝእትነ"፡ "እግዚአብሔርታችን" እንጂ፡ "እመቤታችን" ማለት አይደለም፤ ከመስከረም ፩ ቀን፡ የርእሰ ዐውደ-ዓመት በዓል ጋር፡ ዐብሮ ስለሚታሰበው፡ ስለእግዚአብሔር እም፡ ድንግል ማርያም፡ የልደቷ በዓል፡ እዚህ ላይ፡ ሊታወስ የሚገባው ቍም-ነገር አለ። ያንንም፡ እንደሚከተለው ገላልጠን አቅርበንላችኋል፦ መልእክቱን በሙሉ ለመከታተል፡ እንደሚከተለው ይቀጥሉ!... |
የኢየሱስ ክርስቶስን በዓለ ሆሣዕና እና በዓለ ትንሣኤ፡ ክርስቲያኑ ዓለም፡ በያመቱ፡ እያከበረ ያለው፡ እንዴት ነው? በእውነት ነውን? ለሰው ልጆች መልካም ሕይወት፡ ጠንቅ የኾነው ጥያቄ፡ አጥጋቢዉን የመፍትሔ መልስ: ለአንዴና ለመቼውም ጊዜ አግኝቷል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፡ ከሙታን ተለይቶ ከተነሣ በኋላ፡ እስካረገባት ዕለት ድረስ፡አርባ ቀን ሙሉ፡ ምን ሲያደርግ ቆየ? ለቅዱሳንና ለቅዱሳት አማኞቹ ሓዋርያት እየተገለጠላቸው፡ ስለኢትዮጵያ፡የእግዚአብሔር መንግሥት ሲነግራቸውና ሲያስተምራቸው ነዋ! የቅዱስ ኪዳኗ ኢትዮጵያ ኪዳናውያንና ኪዳናውያት ልጆች፡ እነዚህንና ሌሎቹን በዓላት የሚያከብሩበት: ትክክለኛው የሃይማኖትና የምግባር ሥርዓት። ሙሉውን ምንባብ ለመመልከት፡ እንደሚከተለው ይቀጥሉ! ... |
ቸሩ እግዚአብሔር፡ እንኳን፡ለ፳፻፲፭ (፪ሺ፲፭)ኛው ዓመተ-ምሕረት፡ በዓለ-ትንሣኤ፡ በያለንበት አደረሰን! ይድረስ፦ በምድርና በሰማያት በመላችው፡ በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ዕቅፍ ውስጥ፡ የእግዚአብሔርና የኢትዮጵያ ልጆች፣ ነጋሢዎችና ካህናት ኾናችሁ፥ «ኢትዮጵያ» በተባላችው የዐፅመ ርስት አገራችሁ ሠፍራችሁ፥ በኪዳናዊው ኢትዮጵያዊ የጨውነት ህልውናችሁና የመብራትነት ተልእኳችሁም፡ አልጫና ጨለማ በኾነው፡ በዓለሙ ኹሉ አህጉራት፡ በመለኮታዊው ዕቅድ ተዘርታችሁና ተሠራጭታችሁ፣ ተልካችሁና ተመድባችሁ፡ በቀዳማዊቷ የትንሣኤና በዘለዓለማዊቷ የሰንበት ሕይወት ለምትኖሩ፡ የቅዱሱ ኪዳን ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ወገኖቻችን ለኾናችሁት፡ ኪዳናውያን ወንድሞችና ኪዳናውያት እኅቶች ኹሉ! በያላችሁበት! በእግዚአብሔር አብወእም ድንግል ማርያም፥ በእግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ መሲሕ እና በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ስም፡ ኢትዮጵያዊውን ሰላምታችንን፡ እናቀርብላችኋላን። |