ቍጥር ፲፱/፳፻፱ ዓ. ም.
ቃለ ዐዋድ!
እምኢትዮጵያ፡ ዘመንግሥተ እግዚአብሔር።
የአዋጅ ቃል!
ከኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት።
"መጽሓፍ ቅዱስ"ን በተመለከተ።
በአኹኑ ጊዜ፡ "መጽሓፍ ቅዱስ" የሚባለው፡ የቅዱሳት መጻሕፍት ስብስብ፣ በተለይ፡ ብሉያቱ፡ እውነተኞቹ የእስራኤል ልጆች ሳይኾኑ፡ ራሳቸውን፡ "የእስራኤል ልጆች" የሚሉት፡ ኦሪታውያኑ አይሁድ የጻፉት ስለኾነ፡ የኢትዮጵያ ልጆች መጽሓፍ አይደለም። ይህም እውነታ፡ የገናናዎቹ እና የስመ-ጥሩዎቹ፡ የእነመልከ-ጼዴቅ እና የእነንግሥት ማክዳ፣ እነርሱን የመሰሉትም ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያውያት ዜና- መዋዕል እና ዝክረ-ነገር፡ ተሟልቶ እና ተስተካክሎ የተመዘገበበት ባለመኾኑ ጭምር፡ ተረጋግጦ ይታወቃል።
አዎን! እውነት እውነት እላችኋለሁ! የእኛ የእግዚአብሔር እውነት እና የመንፈስ ቅዱስ ቃሎች የሚጻፉት፡ እየራሳቸውን፡ ሙታን ባደረጉት፡ በሰው ልጆች እጅ እና በድን በኾነው ብራና ላይ ሳይኾን፣ እኛ እግዚአብሔር ራሳችን፡ በመንፈስ ቅዱስ እጃችን፡ በሥነ- ተፈጥሮ ሥርዓታችን በምንከትብባችሁ፣ በእኛ፡ ሕያዋን በኾናችሁት፣ በእናንተ፡ በእያንዳንዳችሁ ውሳጣዊ የሰውነት ሰሌዳ ላይ ብቻ ነው።
ይህ ከመኾኑ የተነሣ፡ የእኛ የእግዚአብሔር የኾነውን ቃል፣ ከእኛ ያገኛችሁትንም ዕውቀት እና ሥርዓት፥ ሃይማኖት እና ምግባር ጭምር፡ ቀድሞም፡ ጠብቃችሁ እና ተከትላችሁ፣ አጽንታችሁ እና ሕይወት አድርጋችሁ የኖራችሁት፣ አኹንም እየኖራችሁ ያላችሁት፣ ወደፊትም የምትኖሩት፡ እናንተው፤ ከእነዚያ የሰው ወገኖች ተለይታችሁ፡ በቅድሚያ፡ "የእግዚአብሔር ልጆች"፣ ቀጥሎም፡ "የኢትዮጵያ ልጆች" የተባላችሁት፣ እናንተ፡ የእኛ የእግዚአብሔር፡ ሕያዋን መጻሕፍት የኾናችሁት፣ አዎን! የቅዱሱ ኪዳን ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያውያት ብቻ ናችሁና፡ ከዚህ ማንነታችሁ እና ምንነታችሁ
ሳትነዋወጹ ልትቀጥሉበት ያስፈልጋችኋል።
ጥያቄዎችና፡ መልስ ኾነው የተጠቃለሉት ዓበይት ቍም-ነገሮች
፩ኛ. ኢትዮጵያዊው ሥርዓተ-አምልኮ፦ የኢትዮጵያው መልከ-ጼዴቅ፡ ኅብስተ-አኰቴት እና ጽዋዓ-በረከት ሥርዓት
፪ኛ. ኦሪታዊው የአይሁድ የአምልኮ ወግ፦ በደም የተበከለው፡ የመሥዋዕታቸው እና የቍርባናቸው አቀራረብ ልማድ
መልእክቱን፡ በሙሉ ለመከታተል፡ እንደሚከተለው ይቀጥሉ!...