ቍጥር ፲፱/፳፻፱ ዓ. ም. ቃለ-ዐዋድ።
Submitted by etkog12 on Sun, 08/20/2017 - 12:23ቍጥር ፲፱/፳፻፱ ዓ. ም. ቃለ ዐዋድ!
እምኢትዮጵያ፡ ዘመንግሥተ እግዚአብሔር።
የአዋጅ ቃል!
ከኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት።
"መጽሓፍ ቅዱስ"ን በተመለከተ።
በአኹኑ ጊዜ፡ "መጽሓፍ ቅዱስ" የሚባለው፡ የቅዱሳት መጻሕፍት ስብስብ፣ በተለይ፡ ብሉያቱ፡ እውነተኞቹ የእስራኤል ልጆች ሳይኾኑ፡ ራሳቸውን፡ "የእስራኤል ልጆች" የሚሉት፡ ኦሪታውያኑ አይሁድ የጻፉት ስለኾነ፡ የኢትዮጵያ ልጆች መጽሓፍ አይደለም። ይህም እውነታ፡ የገናናዎቹ እና የስመ-ጥሩዎቹ፡ የእነመልከ-ጼዴቅ እና የእነንግሥት ማክዳ፣ እነርሱን የመሰሉትም ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያውያት ዜና- መዋዕል እና ዝክረ-ነገር፡ ተሟልቶ እና ተስተካክሎ የተመዘገበበት ባለመኾኑ ጭምር፡ ተረጋግጦ ይታወቃል።