የቅዳሴ ጸሎት፥ ጾመ-ኢትዮጵያ፥ ሰላም-ለኢትዮጵያ፥በዓለ-ኢትዮጵያ፥ ሕዝባዊው እግዚኦታ፥ የኢትዮጵያ፡ የሃይማኖት ጸሎት፥ የኢትዮጵያ፡ የቃል ኪዳን ጸሎት፥ ሰላም ለኪ፥ ጸሎተ እግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ፥ አቡነ ዘበሰማያት፥ ኦ ማርያም እምነ ዘበሰማያት፥ አድኀንከን ሕዝብከ፥ መዝሙር፥ ቡራኬ። ፳፬ ጥር ፪ሺ፱ ዓ.ም. (01/02/2017).

በዓለ-ኢትዮጵያ።

ልዑል እግዚአብሔር፡ ከረዥም ዘመናት በኋላ፡ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ በቅዱሱ ኪዳን የኢትዮጵያ ልጆች፥ በሰማይ እና በምድር ፍጥረታተ-ዓለማቱም ኹሉ፣ በኢትዮጵያዊው የእግዚአብሔር እውነት እና የመንፈስ-ቅዱስ ሥርዓተ-አምልኮ፣ ለ፯ሺ፭፻፱ ዓመታት፡ ከጥር ፳፰ እስከ፴ ቀን ለሚከበረው ለዘንድሮው የ፳፻፱ (፪ሺ፱) ዓመተ-ምሕረቱ    በዓለ-ኢትዮጵያ፣ እንኳን፡ በደኅና እና በሰላም አደረሰን! በያለንበትም፡ ልንቀደስበት በቃን!

መልእክቱን በሙሉ ለመከታተል፡ እንደሚከተለው ይቀጥሉ!...

የበዓለ-ኢትዮጵያ፡ ሥርዓተ-ጸሎት።

በኹለንተናው፡ ሓሤት እና ምስጋና ብቻ የተመላው፣ በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ የቅዱስ ኪዳኗ ኢትዮጵያ ልጆች፡ ለዝንተ-ዓለም ሲገለገሉበትና ሲያገለግሉበት የኖሩት፣ ከበዓለ-ኢትዮጵያ የቅዳሴ ጸሎት በፊት የሚደረገውን፡ ሥርዓተ-ጸሎት፡ ትመለከቷቸው፥ ትገለገሉባቸውም ዘንድ፥ እንሆ! በኅዋ-ሰሌዳችን አሥፍረንላችኋል።

በመቅረጸ-ድምፅ እየተዘጋጀ ያለው፡ የሥርዓተ-ጸሎቱ አቅርቦት፡ ፈቃደ-እግዚአብሔር ኾኖ እንደተጠናቀቅ፡ በተገቢው ሥፍራ እንደሚቀርብላችሁ ከወዲኹ ልናሳውቃችሁ እንወድዳለን።

መልእክቱን በሙሉ ለመከታተል፡ እንደሚከተለው ይቀጥሉ!...