የመስከረም ለቺሳ፡ ''ዩቶፕያ (Utopia)'' የሚለው፡ የሰር ቶማስ ሞር መጽሓፍ፡ ኢትዮጵያኛ የትርጉም ሥራና የምርምር ማስታወሻዎች።
Submitted by etkog12 on Sun, 05/24/2015 - 12:34ይድረስ፦ ለኪዳናውያትና ለኪዳናውያን የኢትዮጵያ ልጆች! ለሌሎቻችሁም፡ የምንባብ ታዳሚዎቻችን ኹሉ!
እኔ፡ ኪዳናዊ ወንድማችሁ፡ ንቡረ-እድ ኤርምያስ ከበደ ወልደ-ኢየሱስ፡ ኢትዮጵያዊ ሰላምታዬን፡ በያላችሁበት፡ በእግዚአብሔር ስም አቀርብላችኋለሁ!
"ለእንግሊዝ መንግሥታዊና ሃይማኖታዊ ተሓድሶ፡ ምክንያት የኾነው፡ የመካከለኛው ዘመን፡ የኢትዮጵያ ሥርዓተ መንግሥትና የሕዝቧ አኗኗር - (ኢ) ዩቶፕያ - የትርጕም ሥራና የምርምር ማስታወሻዎች - እውነተኛው "ሕዳሴ" ወይም "ተሓድሶ"፡ ከምንታዌነት (Dualism)፡ ወደተዋሕዶ (Unity) የሚደረግ፡ ኹሉን አቀፍ ኅብረተሰባዊ የንስሓ ጕዞ መኾኑን የሚያሳይ፡ ተጨባጭ እና ታሪካዊ ማስረጃ" በሚል አርእስት፡ በኪዳናዊት መስከረም ለቺሣ ተደርሶ፡ በ፳፻፮ ዓመተ ምሕረት የታተመውንና በሥርጭት ላይ የሚገኘውን መጽሓፍ አነበብሁት።