የ፪ሺ፰ ዓመተ ምሕረት የሕማማት መልእክትና ሥርዓተ ጸሎት።
Submitted by etkog12 on Wed, 04/20/2016 - 16:40ፈጣሪያችንና አምላካችን ኢየሱስ መሲሕ፡ ከማትለየው፡ ቅድስት እናቱና እናታችን ድንግል ማርያም ጋር፡ አስቀድሞ፡ ጾመ-ኢትዮጵያን፥ አከታትሎም፡ ዓቢይ-ጾምን አስፈጽሞ፡ ለዘንድሮው በዓለ-ሆሣዕናና ሰሙነ ሕማማት፡ እንኳን፡ በደኅና አደረሰን!
የ፪ሺ፰ ዓመተ ምሕረት የሕማማት መልእክትና ሥርዓተ ጸሎት።
ይድረስ፡- በምድርና በሰማያት በመላችው፡ በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ፡ የእግዚአብሔርና የኢትዮጵያ ልጆች፥ ነጋሢዎች እና ካህናት (የአገልግሎት ባልደረቦች)፥ ዜጎችም ኾናችሁ፡ “ኢትዮጵያ” በተባለችው አገር ሠፍራችሁ፥ በዓለሙ አህጉራትም ተዘርታችሁ፡ በቀዳማዊቷ የትንሣኤና በዘለዓለማዊቷ የሰንበት ሕይወት ለምትኖሩ፡ "የቅዱስ ኪዳኗ ኢትዮጵያ ልጆች!" ለኾናችሁት ወገኖቻችን!
በእግዚአብሔርና በቅድስት እናቱ ድንግል ማርያም ስም፡ ኢትዮጵያዊውን ሰላምታችንን፡ በያላችሁበት እናቀርብላችኋለን።